አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በመሆን ተመርጠዋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው አቶ ታገሰ ጫፎን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አድርጎ የመረጠው።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት በእጩነት ቀርበው የተመረጡት አቶ ታገሰ ጫፎ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ከቃለ መሃላው በኋላም ተሰናባቿ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ተመራጩ አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

ምክር ቤቱን ለላፉት ወራት በአፈ ጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ሳምንት ያቀረቡትን መልቀቂያ ምክር ቤቱ መቀበሉ ይታወሳል።

መልቀቂያውን ተከትሎም ወይዘሮ ሙፈሪያት አዲስ ለተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወቃል።

 

© 2020 Sidama Media Network All rights reserved.