አላማጣ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተነገረ

የራያ “የማንነት ጥያቄ አለን” ብለው በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኣላማጣ ከተማ ትናንት ሰልፍ በወጡ ወጣቶችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።

ሕይወት የጠፋው ሰዎቹ በጥይት ተመትተው መሆኑን ከአላማጣ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የክልሉ ምክር ቤት የአካባቢው እንደራሴዎች “የአላማጣ ህዝብ ያለው ጥያቄ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንጂ የማንነት አይደለም” ብለዋል።

በግጭቱ ውስጥ የተሣተፉ አካላት ሕግ ፊት እንደሚቀርቡ የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

© 2020 Sidama Media Network All rights reserved.