Sidama Media Network (SMN) ሥራ መጀመሩን አስመልክቶ ከቦርድ ኣባላት የተሰጠ መግለጫ

የሲዳማ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ትላልቅ ብሄሮች ኣንዱ ሲሆን በህዝብ ብዛት ከኦሮሞ ኣማራ ሱማሌና ትግራይ ቀጥሎ ኣምስተኛ ቦታ ይዞ የሚገኝ ታላቅ ሕዝብ ነው። በእኮኖሚዉም የሲዳማ ሕዝብና ኣካባቢ በአገር ደራጃ ከፍተኛውን ድርሻ ከሚያበረክቱ ክልሎች ይመደባል። ለምሳሌ ያህል የዉጪ ምንዛሪ በማስገኘት የመጀመሪያዉን ደረጃ ይዞ የሚገኘዉ ቡና በዋናነት የሚመረተው ሲዳማ ዉስጥ መሆኑን መጥቀስ ይቻላል። ነገር ግን የሲዳማ ህዝብ  እንደ ብዛቱም ሆነ እንደ ኢኮኖሚያዊ ኣስተዋጽዖው የሚመጥነውን ቦታ እያገኘ ኣይደለም። ባህሉ እየተረሳ፤ ትዉልድ እየጠፋ፤ ወጣቱ በመረጃ እጦት የኣስተሳሰብ ደሃ እየሆነ ይገኛል።

 

የሲዳማ ሕዝብ ሃሳቡን ኣመለካከቶችኑና እይታዎቹን በነፃነትና በበቂ ሁኔታ ለህዝብ የሚያደርስበት ሚድያ ባለመኖሩ እነዚህ ችግሮች እየተባባሱ ይገኛሉ። ዛሬ  አለማችን  በኢንፎርሜን ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም መጥቃ እየተጓዘች ባለችበት ዘመን የሲዳማ ሕዝብ  የራሱ የሆነ የራዲዮ ስርጭትም ሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሲዳሚኛ ቋንቋ አለመኖራችዉ በሕዝባችን የእድገት ጎዳና ላይ የፈጠረዉ ጫና እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን መገመት ከባድ አይደለም።

 

ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸዉ በዉጪ ኣገር የሚኖሩ የሲዳማ ቢሄር ተወላጆች 19/05/2018 ባካሄዱት አጠቃላይ ጉባኤ ሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ እንዲቋቋም በሙሉ ድምጽ ዉሳኔ አስተላልፈዋል።

 

በእለቱ ጉባኤዉ SMN ቦርድ ኣባላት በመምረጥና አስፈላጊዉን የገንዘብ ድጋፍ በማድርግ SMN በኣስቸኳይ ሥራዉን እንዲጀምር በወሰነዉ መሰረት፣ ሰኔ 08/2018 መደበኛ ስራዉን እንደሚጀምር ቦርዱ በጉጉት ለሚጠብቁት SMN ቤተሰቦች፤ ለሲዳማ ሕዝብና ኣማራጭ የመረጃ ምንጭ ለሚሹ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ሲያሳዉቅ በህዝባችን ድጋፍ የተጣለበትን ትልቅ ሃላፊነት በሲኬት እንደሚወጣዉ ሙሉ በሙሉ በመተማመን ነው።

 

ለሲዳማ ህዝብ ትክክለኛ፣ያልተዛባ፣ፈጣን ዜናና የተለያዩ ለሕዝቡ ጠቃሚ መረጃዎችን ማድርስ ተቀዳሚ ኣላማዉ ቢሆንም በተላያዩ ዘርፎችም ሳይታግት ከሚሰራቸዉ ህዝባዊ ጉዳዮች የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል:

 

ለየትኛዉም የፖለቲካ አመለካከት ሳይወግን የተለያዩ አመለካከቶች ያላቸዉን ምሁራን ፣ታዋቂ ግለሰቦችንና የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስተናግድ ሕዝቡ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ፣

 

በጥናት ላይ የተመሰረቱ  ትምህርታዊ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ጤና ነክና የተለያዩ ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ በሚባሉ ኣርእስቶች ላይ ሕብረተሰቡን ማወያየትና መረጃዎችን ማቅረብ፣

 

የሲዳማ ሕዝብ ለሁሉም እኩልና ዲሞክራሲያዊ የሆነች አገር ግንባታ ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወት በማገዝ የምንወዳት ኣጋራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክረሲና ፍትህ እንዲሰፍን የሕዝባችንን ድምጽ በማሰማት ሰፋ ባሉ ኣገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይም የሕዝቡ ተሳተፎ ከፍ እንዲል በትጋት መሥራት።

 

በመሆኑም SMN በሕዝብ የተቋቋመ ለስፊዉ የሲዳማ ሕዝብና ለሎች ኢትዮጵያውን ወገኖቹ የሚሠራና ነጻ ሚድያ መሆኑን በዝህ አጋጣሚ ለደጋፊዎቻችንና መላዉ ሕዝባችን እያስታወቅን SMN ጥንካሬ በእናንተ ተሳትፎና ድጋፍ  የሚወሰን በመሆኑ ድጋፋችሁ እንዳይለየን በኣክብሮት እንጥይቃለን።

 

SMN የራሱ የሆነ የሳተላይት ስርጭት መስመር እስኪኖረዉ ለጊዜዉ OMN ጋር በመተባበር በሳምንት ሁለት ቀን ማለትም ሰኞና ኣርብ በሲዳምኛ ቋዋንቋ ፕሮግራም ያሰራጫል። በዚህ ኣጋጣሚ OMN ላደረገልን ትብብር ከፍ ያለ ምስጋና ማቅርብ እንወዳለን። በተጨማሪ SMN ድረ ገጽ፣ ፌስቡክ ገጻችንና፤ ዩትዩብ ቻናላችን ላይ የተለያዩ ፕሮግራሞችም ይቀርባሉ። በኣጭር ጊዜ ዉስጥም የኣማሪኛ ፕሮግራም እንደምንጀምር ልናሳዉቅ ኢንፈልግላን።

 

በመጨረሻም ይህ ታላቅ ፕሮጀክት እንዲሳካ የሁላችሁም አስተዋጸኦ  ወሳኝ ሚና እንድሚኖረዉ በድጋሚ  እያስታወስን ከጎናችን አንድትቆሙና በተለያየ መንገድ ኣስፈጊውን ድጋፍ ሁሉ እንድታደርጉልን ጥርያችንን እናቀርባለን።

 

 SMN ቦርድ ኣባላት።

 

 June 8, 2018

© 2020 Sidama Media Network All rights reserved.