ለሲዳማ ሚድያ ነትዎርክ ቦርድና ሥራአስፈፃሚ ኮሚቴ የደስታ መግለጫ

 የሲዳማ ጥናትና ልማት ኮርፖረሽን  ኣዲስ ለተመሠረተዉ  የሲዳማ  ሚድያ ነትዎርክ ከኦሮሞ  ሚድያ ነትዎርክ ጋር  በመተባበር  ለምያከናዉናቸው  ተግባራት  የደስታ መልእክታችንን ስናስተላልፍ  በዚህም ለሚስጠው ኣገልግሎት ወሳኝና ሙያዊ ብቃትና  እውነታ  ያማከለ ከሆነ ያማረና ዘላቂነት ያለው ሊሆን  እንደምችል እናምናለን።   ይህም ለወገኖቻችን ሲዳማ ህዝብ ማወቅ  የምገባውን ባለማወቅ ልደርስ የምችለውን ክፍተት በመሙላት የተሟላ  ያደርገዋል። በመሆኑም የሚከተሉትን ማስታዎስ  እንዎዳለን።   ይኸውም በጉዞ ላይ እንቅፋቶች ልኖሩ ስለምችሉ ይህንን በበጎ ማየት እንጂ ኣዳጋች ሆኖ መታየት የለበትም።  ኣንድ ፀሃፍ እንዳለው “ እርምጃ  ለዕድገት ፍሬ  ነው፤ ተግባር  ግን ወደግባችን ይወስደናል “ ይላል።   በመሆኑም  ለእድገታችን ምንም ልያገዳችሁ  ኣይችልም።  የ ሲዳማ ጥናትና ልማት  ኮርፖረሽን በማናቸውም  ጊዜ ከጎናችሁ መሆኑን  እናረጋግጣለን።

 በድጋሚ  እንኳን ደስ ኣለን።

 የሲዳማ  ጥናትና ልማት ኮርፖረሽን  ቦርድና ሥራአስፈፃሚ ኮሚቴ

ግንቦት 30/2010

© 2020 Sidama Media Network All rights reserved.