የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ መቋቋሙን አስመልክቶ ከሲዳማ ኮሙኒትይ ዎርልድ ዋይድ የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ

ሚዲያ ለአንድ ሕዝብ እድገት ከሚያስፈጉ መሰረታዊ ትቋማት የመጀመሪያዉን ቦታ ይዞ
እንደሚገይኝ አጠያያቂ አይድለም።እስካሁን ድረስ ሰሲዳማ ሕዝብ የራሱ የሆነ ሚዲያ
አለመኖሩ ሕዝባችን ከድህነት ለመላቀቅ በሚያደርገዉ ትግል ከፍተኛ ኣሉታዊ አስተዋጸኦ
አበርክቶአል።በመሆኑም በዛሬዉ ቀን የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ በመመስረቱ የተሰማንን
ጥልቅ ደስታ በኣባሎቻችን ስም ለመግልጽ እንወዳለን።

የሲዳማ ኮሙኒቲ ዎርልድዋይድ ከፖላቲካ ነጻ በሆነ መልኩ በተለያዩ ዘርፎች የሲዳማን
ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል የሚሰራ ሲሆን ይህንን ኣላማ ከግቡ ለማድረስ ከሲዳማ ሚዲያ
ነትዎርክ ጋር በመተባበር እጅ ለእጅ ተያይዞ እንድሚሰራ ያለው ተስፋ ከፍ ያለ ነው።

በመሆኑም ዛሬ የምትጀምሩት ሥራ የተሳካ እንዲሆንላሁ ከፍ ያለ ምኞታችንን እያገለጽን
የሲዳማን ሕዝብ ከኃላቀርነትና ከድህነት ወጥመድ ለማስወጣ በሚደረገዉ ትግል ግንባር
ቀደም ሚና እንድምትጫወቱ ያለን ተስፋ እጅግ የላቀ ነዉ። ይህም ተግባራዊ ሊሆን
የሚችለዉ አንድ የሚዲያ ተቋም ሁሉንም ያገባኛል የሚሉትን ኣካላት ምንም ኣይነት
ወገናዊነት በሌሌዉ መልኩ ማስተናገድ ሲችል በመሆኑ ይህንን ሕዝባዊ ኣደራ ከፍተኛ
ኃላፊነት በተሞላዉ መልኩ እንደምትወጡ ጽኑ እምነት እንዳለን ልንገልጽላችሁ
እንወዳለን።

ሞገስ መርድ ዱባለ
የሲዳማ ኮሙኒቲ ዎርልድዋይድ ፕሬዝደንትነት

Related Topics
© 2020 Sidama Media Network All rights reserved.